የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክስዮን ማህበር ባለአክስዮኖች በሙሉ

እጩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የኢንሹራንስ ሥራ አዋጅ ቁጥር 746/2ዐዐ4, የሪኢንሹራንስ ማቋቋሚያ ዳይሬክቲቭ በቁጥር SRB/1/2014 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SIB/48/2019 እና የኩባንያውን የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ የዕጩዎች ማቅረቢያና ማስፈፀሚያ መመሪያ (ማሻሻያ ቁጥር 1) መሠረት በማድረግ በቀጣይ ኩባንያውን በቦርድ አባልነት የሚመሩ አባላትን ለማስመረጥ በታህሳስ 11 ቀን 2ዐ16 ዓ.ም. በተካሄደው የባለአክሲዮኖች 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተቋቋመው የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ እጩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ባለአክስዮኖች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እጩ የቦርድ አባላትን እንድትጠቁሙ አስመራጭ ኮሚቴው በአክብሮት ይጋብዛል፡፡ መስፈርቶቹም፡-

1ኛ/  የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክስዮን ማህበር ባለአክስዮን የሆነ/ች እና ቢመረጥ/ብትመረጥ በዲሬክተሮች ቦርድ አባልነት ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/ች፣

2ኛ/  ዕድሜው/ዋ 3ዐ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣

3ኛ/  የትምህርት ደረጃ፡-

ሀ.  ቢያንስ 75% የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ከታወቀ የትምህርት ተቋም ያላቸው፣

ለ.  የቀሩት 25% ቢያንስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

4ኛ/  የሥራ ልምድ፡-

በኢንሹራንስ፣ በሪኢንሹራንስ፣ በፋይናንስ፣ በአካውንቲንግ፣ በሕግ፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በኦዲቲንግ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት እና ሌሎች ተዛማጅነት ባላቸው ሙያዎች ላይ በቂ የሥራ ልምድ ያለው/ያላት መሆን አለበት/ባት፤ (በኢንሹራንስና በሪኢንሹራንስ ልምድ ቢኖራቸው ይመረጣል)

5ኛ/  የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ አባል ያልሆነ/ች ወይም የአክሲዮን ማኀበሩ ተቀጣሪ ሠራተኛ ያልሆነ/ች፣

6ኛ/  የማንኛውም የፋይናንስ ተቋም የዲሬክተሮች ቦርድ አባል ያልሆነ/ች፣

7ኛ/ ተጠቋሚው የሕግ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ ድርጅቱን የሚወክል የተፈጥሮ ሰው ማንነት መግለጽ አለበት/ባት፣

8ኛ/ በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ የዕምነት ማጉደል ወይም የማጭበርበር ተግባር ያልፈጸመ/ች፣ ከመንግሥት አካላት መረጃ ያልደበቀ/ች፣ ለፋይናንስ ተቋማትና ለተቆጣጣሪ አካል ሐሰተኛ መረጃ ያልሰጠ/ች፣ የሥነ-ምግባር ደንቦችን ባለማክበር የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ያልተወሰደበት/ባት፣ በሙስና ወንጀል ተከሶ/ሳ ያልተፈረደበት/ባት፣ ከመምረጥና መመረጥ መብት ያልተገደበ/ች፣

9ኛ/ በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ በማናቸውም በፈረሰ ድርጅት ዲሬክተር፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይም ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚ ያልነበረ/ች ወይም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በሥራ አመራር ላይ ያልተሳተፈ/ች፣

1ዐኛ/ የፋይናንሻል ጤናማነትን መስፈርት የሚያሟላ/የምታሟላ ማለትም በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ በኪሳራ ላይ ያልሆነ/ች፣ የታክስና የባንክ ግዴታዎችን የተወጣ/ች፣ የባንክ ብድር ባለመክፈሉ/ሏ ምክንያት ንብረቱ/ቷ ያልተሸጠ፣ ከማንኛውም የፋይናንስ ተቋም የተወሰደ ጤናማ ያልሆነ ብድር የሌለበት/ባት፣ በደረቅ ቼክ ምክንያት የባንክ ሂሳብ ያልተዘጋበት/ባት፣

11ኛ/ ከሚጠቆሙት እጩዎች መካከል 1/4ኛው ተፅዕኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች (ከአክሲዮን ማኀበሩ የተፈረመ ካፒታል 2% በታች ባላቸው) ብቻ ከተጠቆሙት እጩዎች ውስጥ ይወሰዳሉ፣

12ኛ/ ቀሪዎቹ 3/4ኛ እጩዎች ሁሉም ባለአክስዮኖች ከሚጠቁሙት ውስጥ ይወሰዳሉ፣

13ኛ/ ከላይ የተጠቀሱት መመዘኛዎች እንደተጠበቁ ሆነው ለዲሬክተሮች ቦርድ እጩ አባልነት የሚጠቆም ማንኛውም ባለአክስዮን በብሔራዊ ባንክና በባለአክስዮን ጠቅላላ ጉባኤ ዕምነት የሚጣልበት/ባት፣ ሐቀኛ፣ ጠንቃቃ፣ መልካም ዝናና የተሟላ ስብዕና ያለው/ያላት የአክስዮን ማኀበሩን ዓላማዎችና ራዕይ ለማሳካት በቅንነትና በተነሳሽነት የሚሠራ/የምትሠራ፣ የቦርድ አባል ሆኖ ለመሥራት ቁርጠኛ የሆነ/ች መሆን አለበት/ባት፤

14ኛ/ ተፅእኖ ፈጣሪ የሆኑ ባለአክሲዮኖች እስከ ሰባት እጩዎችን መጠቆም ይችላሉ፡፡

15ኛ/ ተፅእኖ ፈጣሪ ያልሆኑ ባለአክሲዮኖች እስከ ዘጠኝ እጩዎችን መጠቆም ይችላሉ፡

ባለአክስዮኖች ከኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. ዋና መ/ቤት አፍሪካ ጐዳና ቢትወደድ ባህሩ አብርሃም ሕንጻ 6ኛ ፎቅ ለጥቆማ መስጫ በተዘጋጀው ጽ/ቤት ወይም ከአክስዮን ማኀበሩ ድረ-ገጽ www.ethiopianre.com የእጩ ጥቆማ ቅጽ በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 3ዐ ቀን 2ዐ17 ዓ.ም. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የዲሬክተሮች ቦርድ እጩዎችን መጠቆም የምትችሉ መሆኑን አስመራጭ ኮሚቴው በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ባለአክስዮኖች የሞሉትን ቅጽ በአክስዮን ማኀበሩ ዋና መ/ቤት 6ኛ ፎቅ የዲሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ለጥቆማ መቀበያ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ወይም በአክስዮን ማኀበሩ የፖ.ሣ.ቁጥር 12687 ላይ በአደራ ደብዳቤ አድራሻውን ለኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. የዲሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ በማለት ወይም የተሞላውን ቅጽ ስካን በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ኢሜል tsegayeamde504@gmail.com አያይዘው መላክ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ዐ911 229925 እና ዐ911 413696 ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ

  1. አስመራጭ ኮሚቴው ከጥቅምት 3ዐ ቀን 2ዐ17 ዓ.ም. በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን የማይቀበል መሆኑን ከወዲሁ ያሳስባል፣
  2. በቅጹ ላይ የጠቆመው ባለአክስዮን ስምና ፊርማ መኖር አለበት፣ ጠቋሚው ድርጅት ከሆነ የድርጅቱ ዋና ኃላፊ ፊርማና ሕጋዊ ማኀተም ሊኖረው ይገባል፣
  3. ቅጹ ስርዝና ድልዝ እንዳይኖረው በጥንቃቄ መሞላት ይኖርበታል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በተጠቀሰው ስልክ ቁጥር ይደውሉ

ዐ115 575757/ ዐ115 58279ዐ/ ዐ115 582792/ ዐ115 5582793

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክስዮን ማህበር

Ethiopian Reinsurance Share Company

የዲሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኰሚቴ