ለኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. ባለአክሲዮኖች ታህሣሥ 6 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ባካሄዱት 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮጵያ ብሔሪዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SIB/48/2019 መሠረት የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት የመረጡ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ኮሚቴውም ባለአከሲዮኖች ጥቆማ እንዲያደርጉ ባሳወቀው መሠረት ጥቆማዎችን ሲቀበል ቆይቷል፤ የጥቆማ ማቅረቢያ ጊዜውም ተጠናቅቋል፡፡ ስለሆነም አስመራጭ ኮሚቴው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SIB/48/2019 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ከተጠቆሙት መካከል የመረጣቸውንና ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት የተቀመጡትን መመዘኛዎች ያሟላሉ ብሎ ያመነባቸውን ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን እጩዎች ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላነት ምርጫ በእጩነት ያቀረበ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
ተጽእኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክስዮኖች ብቻ ከተጠቆሙት መካከል የቀረቡ እጩዎች |
ተጽእኖ ፈጣሪ በሆኑና ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች በጋራ ከተጠቆሙት መካከል የቀረቡ እጩዎች |
1. አቶ ኃይለማርያም አሰፋ የሺጥላ 2. አቶ እዩኤል እውነቱ ገብረጻዲቅ 3. አቶ ሽፈራው ባንቴ ስለሺ 4. አቶ ተሾመ በየነ በርኸ |
1. አቶ ቀልቤሳ ከራ ቶቦ 2. ወ/ሮ ዙፋን አበበ አለሙ (ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. በመወከል) 3. አቶ ነፃነት ለሜሣ ጉራራ (የኢትዮጵያ መድን ድርጅትን በመወከል) 4. አቶ ጅባት አለምነህ ፉጂ 5. አቶ ካሳሁን በጋሻው ወግደረስ (አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. በመወከል) 6. አቶ ዮናስ ልደቱ ወ/ማርያም (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በመወከል) 7. ወ/ሮ መሠረት በዛብህ አበበ 8. አቶ ንጉሥ አንተነህ ይርሳው 9. አቶ ሙሉነህ አያሌው ጐበዜ (ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በመወከል) 1ዐ. ወ/ሮ ፍሬሕይወት አለማየሁ ቀልቤሳ 11. አቶ ዮናስ ደበበ ተ/ሃይማኖት (አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ በመወከል) 12. አቶ ተምትም ቶላ ጉዳ 13. አቶ አህመድ አቡበከር ሸሪፍ (ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. በመወከል) 14. አቶ ተስፋዬ ምግባር አበበ |
ተጠባባቂ ዕጩ |
|
1. አቶ ተፈራ ወንድሙ ወልደማርያም |
የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ. |