ለኢትዮጵያ ጠለፋ መድን ባለአክሲዮኖች በሙሉ

አክሲዮኖችን በቀደምትነት መብት ለመሸጥ የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማህበር ሲቋቋም የነበረው አክሲዮን ተከፍሎ መጠናቀቁን ተከትሎ ታህሳስ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የኩባንያው የተከፈለ ካፒታል ከብር 997,300,000 ወደ ብር 2,500,000,000 ከፍ እንዲል መወሰኑ ይታወቃል፡፡

የስብሰባው ቃለ-ጉባኤ በብሔራዊ ባንክ እና በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ የተመዘገበ በመሆኑ እያንዳንዱ ነባር ባለአክሲዮን ደንበል አካባቢ በሚገኘው በኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት ቢትወደድ ባህሩ አብርሃም ህንፃ 6ኛ ፎቅ በአካል በመገኘት እና ለዚሁ አላማ የተዘጋጀውን ቅፅ በመሙላት መግዛት የሚፈልገውን የአክሲዮን መጠን እንዲያሳውቅ እንጠይቃለን፡፡

የአክሲዮኑ አሻሻጥ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡-

1ኛ. የአክሲዮኖቹ ሽያጭ የሚጀመረው ሚያዚያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ሲሆን ሽያጩ የሚጠናቀቀው ከ90 ቀናት በኋላ ሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ይሆናል፡፡

2ኛ. አክሲዮኖቹ የሚሸጡት በተፃፈባቸው ዋጋ ነው፡፡

3ኛ. አክሲዮኖቹ እንደተፈረሙ ተከፋይ መሆን የሚገባው ለመግዛት ከተፈለገው የአክስዮን መጠን 25% ማነስ የለበትም፡፡

4ኛ. አክሲዮኖቹ ለመግዛት የቀደምትነት መብት ባላቸው ባለአክሲዮኖች ያልተገዙ ከሆነ እያንዳንዱ ባለአክሲዮን መግዛት የሚፈልገውን ተጨማሪ የአክሲዮን መጠን በተዘጋጀው ቅፅ ላይ መሙላት ይጠበቅበታል፡፡

5ኛ. ኩባንያው ተራፊውን አክሲዮን ለእያንዳንዱ ባለአክሲዮን ባለው የአክሲዮን ድርሻ መጠንና ባቀረበው ጥያቄ ወሰን ይደለድላል፤ የተደለደለውን የአክሲዮን መጠን ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ያሳውቃል፡፡

6ኛ. የሁለተኛው ዙር ድልድል ለእያንዳንዱ ባለአክሲዮን ከተገለፀበት በኋላ ባሉት 30 ቀናት መፈረም እና 25% ክፍያውም ከሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ መጠናቀቅ አለበት፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ አክሲዮን አስተዳደር ክፍል ስልክ ቁጥር         0115-575757 የውስጥ መስመር ቁጥር 107 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር