የስብሰባ ጥሪ

ለኢትዮጵያ ጠለፋ መድን .. ባለአክሲዮኖች በሙሉ

10 መደበኛ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንግድ ህግ ክፍል 2 አንቀጽ ቁጥር 366፣ 367፣ 370፣ 371፣ 372 እና 393 እንዲሁም 400 መሠረት፣ የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አ.ማ የባለአክሲዮኖች 10ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ማክሰኞ ታህሣሥ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 83 ሰዓት ጀምሮ በሂልተን ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሠው ቀንና ሰዓት በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የዲሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

  • የማህበሩ የተፈረመ ካፒታል፣ ብር 2,500,000,000.00
  • የማህበሩ የተከፈለ ካፒታል፣   ብር 2,449,171,266.00
  • ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሠጠ የሥራ ፈቃድ ቁጥር RB/01/2016
  • የማህበሩ የንግድ ምዝገባ ቁጥር፣  MT/AA/3/0035454/2008
  • የማህበሩ አድራሻ፣  ከተማ፡   አዲስ አበባ ፣ ክ/ከተማ፡  ልደታ ፣  ወረዳ፡  9 ፣  የቤት ቁጥር፡  አዲስ
  • የማህበሩ ድረ-ገጽ www.ethiopianre.com
የ10ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
  1. ከ9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በኃላ የተደረጉ የአክሲዮን ዝዉዉሮችን ማሳወቅ እና አዲስ ገቢ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፤
  2. ከተጠባባቂ የቦርድ አባላት የተተኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ለጠቅላላ ጉባኤ ማሳወቅ እና ማፀደቅ፤
  3. እ.ኤ.አ. የ2024/25 የሂሳብ አመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
  4. እ.ኤ.አ የ2024/25 የሂሳብ አመት የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
  5. እ.ኤ.አ. የ2024/25 የሂሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ ድልድል እና ክፍፍል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  6. እ.ኤ.አ. የ2025/26 የሂሳብ ዓመት የዉጭ ኦዲተሮች የአገልግሎት ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሠን፤
  7. እ.ኤ.አ. የ2024/25 የሂሳብ አመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አመታዊ የአገልግሎት ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  8. እ.ኤ.እ. የ2025/26 የሂሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልን ተወያይቶ መወሠን፤
  9. በ9ኛው የባለአክሲዮኖች አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተደረገው የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ ጋር ተያይዘዉ የነበሩ ጉዳዮችን ለባለአክሲዮኖች ማሳወቅ፤
  10. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፤
የ5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
  1. የማህበሩን የመመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻል፤
  2. የማህበሩን ካፒታል በተከፈለዉ የካፒታል መጠን መሰረት ማሻሻል፤
  3. የማህበሩን ካፒታል ማሳደግ፤ 
  4. የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፣

ማሳሰቢያ፡

  • ባለአክስዮኖች በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ከሆነ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጆስ ሀንሰን አካባቢ በሚገኘዉ፣ የኢትዮ ሪ-ሀውስ ህንፃ 6ኛ ፎቅ የኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት ከስብሰባው ዕለት ቢያንስ ከ15  ቀን ጀምሮ በአካል በመገኘት የውክልና ቅጽ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  • በኩባንያው ቀርባችሁ ውክልና የምትሠጡም ሆነ በጉባኤው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚያሳይ የታደሠ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንዲሁም በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ህጋዊ ውክልና ይዛችሁ የምትሣተፉ ተወካዮች የወካያችሁን ማንነት የሚያሳይ የታደሠ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
  • በውል አዋዋይ የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ ማስረጃውን እና ከፒውን ይዞ በመቅረብ በስብሰባው ላይ መሣተፍ ይችላል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር

ዐ115 575757/ ዐ115 58279ዐ/ ዐ115 582792/ ዐ115 582793 ይደውሉ                                                            

የዳይሬክተሮች ቦርድ

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን ..